lirik.web.id
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

lirik lagu tedy afro – ፀባዬ ሰናይ (tsebaye senay)

Loading...

ደሞ እንድነቃ ዳግም ቆሜ
አትመላለሽ መተሽ በልሜ
የቀኑ ማማር ይበቃሻል
ከተኛው አይኔ ምንቀርቶሻል

አያንስም ለኔ ያንቺ ገላ
ከፈርኦን ልጅ ከገሊላ
ፍቅርሽ ባይሰጥም አሳልፎ
አስቀርቶታል ልቤን ጠልፎ

ዛሬስ መወደድ ላንቺ ነግቶልሻል
የውበት ፀሀይ ወቶልሻል
አዬ ጀምበር ሞላ አለም አጎንብሳ
ያይንሽን ብሌን ውሀ ለብሳ

ገጥሞሽ የሳባ ሞገስ የኪሊዮፓትራ
አምረሽ ትታዪ ጀመር በራስሽ ተራ
ባለም የውበት ፀሀይ ወቶ እንደገና
ባንቺ ዘመን ላይ ዋለ ዛሬ ቁንጅና

ያንስብሻል መባል ቆንጆ የማር ክዳኔ
ከንፈርሽ ላይ ሰም አለ ወርቅ የፍቅር ቀኔ
ያንስብሻል የኔ መልካም ያመል ሙዳይ
ሰው አለወይ ውብ እንዳንቺ ፀባዬ ሰናይ

አለወይ (ፀባዬ ሰናይ)
አለወይ (ፀባዬ ሰናይ)
አለወይ (ፀባዬ ሰናይ)
አለወይ (ፀባዬ ሰናይ)
ውብ እንዳንቺ ፀባዬ ሰናይ
(ውብ ፀባዬ ሰናይ ሰናይ)
ሰናይ
ፀባዬ ሰናይ
ሰናይ

ደሞ እንድነቃ ዳግም ቆሜ
አትመላለሽ መተሽ በልሜ
የቀኑ ማማር ይበቃሻል
ከተኛው አይኔ ምን ቀርቶሻል

አያንስም ለኔ ያንቺ ገላ
ከፈርኦን ልጅ ከገሊላ
ፍቅርሽ ባይሰጥም አሳልፎ
አስቀርቶታል ልቤን ጠልፎ

ዛሬስ መወደድ ላንቺ ነግቶልሻል
የውበት ፀሀይ ወቶልሻል
አዬ ጀምበር ሞላ አለም አጎንብሳ
ያይንሽን ብሌን ውሀ ለብሳ

ሆነሽ በመልክሽ ገዳይ የውበት አርበኛ
ማሰብ አቃተን ባንቺ ተማርከን እኛ
ወጥተን ባለም ከፍታ ምድሪቱን ባናይ
የለም እንዳንቺ ቆንጆ ፀባዬ ሰናይ

ያንስብሻል መባል ቆንጆ የማር ክዳኔ
ከንፈርሽ ላይ ሰም አለ ወርቅ የፍቅር ቅኔ
ያንስብሻል የኔ መልካም ያመል ሙዳይ
ሰው አለውይ ውብ እንዳንቺ ፀባዬ ሰናይ

አለወይ (ፀባዬ ሰናይ)
አለወይ (ፀባዬ ሰናይ)
አለወይ (ፀባዬ ሰናይ)
አለወይ (ፀባዬ ሰናይ)
ውብ እንዳንቺ ፀባዬ ሰናይ
(ውብ ፀባዬ ሰናይ ሰናይ)
ሰናይ
ፀባዬ ሰናይ
ሰናይ
ፀባዬ ሰናይ
ሰናይ


Lirik lagu lainnya:

LIRIK YANG LAGI HITS MINGGU INI

Loading...