lirik lagu tedy afro – ኢትዮጵያ (ethiopia)
ባልፍም ኖሬ
ስለ እናት ምድሬ
እሷናት ክብሬ
ኸረ እኔስ አገሬ
ባልፍም ኖሬ
ስለ እናት ምድሬ
እሷናት ክብሬ
ኸረ እኔስ አገሬ
ስንት የሞቱለሽ ለክብርሽ ዘብ አድረው
አልፈው ሲነኩሽባህርሽን ተሻግረው
የጀግኖች አገር ያዳም እግር አሻራ
ፈለገ ጊዎን ያንች ስም ሲጠራ
እንኳ ሠማይ ላይ ባንዲራሽን አይቶ
ስምሽ ሲጠራ ማን ዝም ይላል ሠምቶ
እንኳን ሠማይ ላይ ባንዲራሽን አይቶ
ኢትዮጲያ ሲባል ማን ዝም ይላል ሰምቶ
ኦሆሆ ሆሆ አ…
በቀስተ ዳመናሽ ሰማይ መቀነቱን ባንዲራሽን ታጥቆ
አርማሽ የታተመ እንኳን ባለም መዳፍ በአርያም ታውቆ
የተራሮች አናት ዘብ የቆመልሽ ቤት ያክሱማ ራስ ጦቢያ
የፍጥረት በርነሽ የክብ አለም ምዕራፍ ዞሮ መጀመሪያ
በሠማዩ ላይ ቢታይ ቀለም
የሷ ነው እንጂ ሌላ አይደለም
የመጪው ዘመን ፊት ናት መሪ
ዛሬ አለም ቢላት ኋላ ቀሪ
ተውኝ ይውጣልኝ ልጥራት ደጋግሜ
ኢትዮጲያ ማለት ለኔ አይደል ወይ ሥሜ
ቢጎል እንጀራው ከመሶቡ ላይ
እናት በሌላ ይቀየራል ወይ
ይዤ አላነሳም እጄን ከቀሚሷ
እናት እኮ ናት ተስፋ አልቆርጥም በሷ
የሷን ውለታ ከፍሎ ሳይጨርስው
ኢትዮጵያ ሲባል አብሮ አይልም ወይ ሰው
ኢትዮጵያ (ኢትዮጵያ)
ሀገሬ (ሀገሬ)
ኢትዮጵያ (ኢትዮጵያ)
ሀገሬ (ሀገሬ)
ባንቺ አይደል ወይ ክብሬ
ባልፍም ኖሬ
ስለ እናት ምድሬ
እሷናት ክብሬ
ኸረ እኔስ አገሬ
ስንት የሞቱለሽ ለክብርሽ ዘብ አድረው
አልፈው ሲነኩሽባህርሽን ተሻግረው
የጀግኖች አገር…
Lirik lagu lainnya:
- lirik lagu luke rainsford – father’s day
- lirik lagu haze76 – leise
- lirik lagu between nothing – windless one
- lirik lagu nipsey hussle – dedication
- lirik lagu irv da phenom – moment 4 life
- lirik lagu električni orgazam – gde smo sad?
- lirik lagu seb la frite – métamorphose
- lirik lagu mistur – distant peaks
- lirik lagu oriente – a mochila
- lirik lagu too $hort – quit hatin’, part 2