lirik lagu ቴዎድሮስ ካሳሁን(teddy afro) – ናት ባሮ (nat baro)
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ናት ባሮ የወንዙ ዳር ኗሪ
አጊጣ ባልቦ መሳይ ድሪ
ሁሌ ላያ’ት እንዳዲስ ገራሚ
ናት የባሮ የወንዙ ዳር ሎሚ
ናት ባሮ የወንዙ ዳር ኗሪ
አጊጣ ባልቦ መሳይ ድሪ
ሁሌ ላያ’ት እንዳዲስ ገራሚ
ናት የባሮ የወንዙ ዳር ሎሚ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ጥቁሯ ወርቅ ቀጥ እንደ ሸምበቆ
አኳሆኗ በአታሞ ምት ረቆ
ፍቅር ሲሞቅ እሳት ነዶ ማታ
ውበት አየሁ ዳንኪራ ሲመታ
ያበቀላት የወንዙ ዳር ኑሮ
ናት የባሮ
ቶም ሰርታ በዣንጥላው ብረት
በጨረቃ ፍቅርን ያዜምንበት
የታንኳው ላይ የወንዙ ሽርሽር
እረፍት አጣው ትዝባለኝ ቁጥር
ያበቀላት የወንዙ ዳር ኑሮ
ናት የባሮ
ናት ባሮ ናት ባሮ የወንዙ ዙሪያ ሴት
የገዛችው የልቤን ውስጥ ስሜት
ናት ባሮ ናት ባሮ የወንዙ ዳር ቆንጆ
የሰራችው በልቤ ላይ ጎጆ
መሸት ሲል ጀምበር አዘቅዝቆ
ቀዩን ሰማይ ውሃው አንፀባርቆ
እያየሁዋት በጨረቃ መብራት
አማረኝ የታንኳ ላይ እራት
ጉድ አረገኝ በውበት ሳር አስሮ
አየ ባሮ
ናት ባሮ ናት ባሮ
የወንዙ ዙሪያ ሴት
የገዛችው የልቤን ውስጥ ስሜት
ናት ባሮ ናት ባሮ
የወንዙ ዳር ቆንጆ
የሰራችው በልቤ ላይ ጎጆ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ይሄ ልቤ የሆነብኝ ምነው
ሀሳቤም ሁሌ ከአዊሊ ነው
ልያት እንጂ ወይ ሄጄ ዳግመኛ
ባደርጋት የሁሌ ጓደኛ
አሳ ሆኖ ልኮኝ እንጀራዬ
ከአዲስ አበባው የትውልድ አምባዬ
ተመለስኩኝ በፍቅሯ ተይዤ
የሸገር ልጅ ባዶ ቅርጫት ይዤ
ኚላል ባድ ኦፔኖ … አገነ ገቲያ
ኚላል ባድ ኦፔኖ … አነ ሚየጎ
ኚላል ባድ ኦፔኖ … አጀሎየ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ናት ባሮ … አሳ አጠምድ ብሎ
ናት ባሮ … ዘርግቶት መረቡን
ናት ባሮ … እንዴት ለቆንጆ ሴት
ናት ባሮ … ሰው ይጥላል ልቡን
ናት ባሮ … አይኔ እሷ ላይ ቀርቶ
ናት ባሮ … አሳ አጣሁ ለእራቴ
ናት ባሮ … ባዶ ቅርጫት ይዤ
ናት ባሮ … ተመለስኩኝ ቤቴ
ናት ባሮ ናት ባሮ
የወንዙ ዙሪያ ሴት
የገዛችው የልቤን ውስጥ ስሜት
ናት ባሮ ናት ባሮ
የወንዙ ዳር ቆንጆ
የሰራችው በልቤ ላይ ጎጆ
ኚላል ባድ ኦፔኖ … አገነ ገቲያ
ኚላል ባድ ኦፔኖ … አነ ሚየጎ
ኚላል ባድ ኦፔኖ … አጀሎየ
ኚላል ባድ ኦፔኖ… (ጋምቤላ)
ኚላል ባድ ኦፔኖ … አገነ ገቲያ
ኚላል ባድ ኦፔኖ … አነ ሚየጎ
ኚላል ባድ ኦፔኖ …
Lirik lagu lainnya:
- lirik lagu jason derulo – talk with your body (demo)
- lirik lagu lindsay mccaul – where do you go
- lirik lagu red warrior – trap star
- lirik lagu urbánse – si se calla el cantor
- lirik lagu robin trower – little bit of sympathy
- lirik lagu the wordshipper – checkmate
- lirik lagu willow beats – don’t even ask
- lirik lagu a.r – chapitre 3
- lirik lagu amos lee – walls
- lirik lagu rihanna – sos (music video version)