lirik.web.id
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

lirik lagu rophnan - hiwot

Loading...

በጋ ዝናብ ሲቀርበው
ህይወት ሐሙስ ሲቀረው
ሰውም የሄደ ቀን ነው ′ሚወደደው

ባለቀን ሲመሽበት
ባለኪስ ሲጎድልበት
ነገር ሁሉ ይታወቃል ያጡት ዕለት

እኔም ልውደድሽ በቃህ እንዳልሺኝ
ከጎኔ እንደተለየሺኝ
ዛሬ አጠገቤ ነሽ አውቃለሁ
ግን እንዳጣሁሽ እወድሻለሁ

እወድሻለሁ
እወድሻለሁ
እወድሻለሁ ህይወት!
እወድሻለሁ
እወድሻለሁ
እወድሻለሁ ህይወት!

አይ ህይወት!
አንቺ ህይወት በጋ ዝናብ ሲቀርበው
ጀግናም አፈር ሲቀምሰው
ሰውም የሞተ ዕለት ነው ‘ሚወደሰው
አፍቃሪው ሲል ይበቃል
ተፈቃሪው ይነቃል
ሰው እድሜው ሲመሽ እግዜር ማለት ያበዛል
ህይወት ላፍቅርሽ ሳይመሽብኝ
መውደዴ ግድ ሳይሆንብኝ
ዛሬ እጄ ላይ ነሽ አውቃለሁ
ግን እንዳጣሁሽ እወድሻለሁ

እወድሻለሁ
እወድሻለሁ
እወድሻለሁ ህይወት!
እወድሻለሁ (እወድሻለሁ)
እወድሻለሁ (እወድሻለሁ)
እወድሻለሁ ህይወት!
አይ ህይወት!

አይ ህይወት!
ሳላጣሽ
አሁን አሁን ልውደድሽ ልውደድሽ!!!
ልውደድሽ አሁን ልውደድሽ


Lirik lagu lainnya:

LIRIK YANG LAGI HITS MINGGU INI

Loading...