lirik.web.id
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

lirik lagu mesfin gutu - yalayehut alem

Loading...

የተደረገልኝን ፡ አይቼ
ከአንተ ፡ የተቀበልኩትን ፡ አይቼ
በፊትህ ፡ ቅኔን ፡ ተቀኘሁኝ

እንዲህ ፡ አልኩኝ

አንተ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ አንተ
ኧረ ፡ አንተ ፡ ንጉሤ ፡ ነህ ፡ አንተ
አንተ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ አንተ
ኧረ ፡ አንተ ፡ አባቴ ፡ ነህ ፡ አንተ

ያላየሁት ፡ ዓለም ፡ ያልቀመስኩት ፡ ኑሮ
በጌታ ፡ ሆነልኝ ፡ ይገርማል ፡ ዘንድሮ
ተመስገን ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ይባላል
የአምላኬ ፡ ቅናት ፡ ይህንን ፡ አድርጓል
ተመስገን ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ይባላል
የአምላኬ ፡ ቅናት ፡ ይህንን ፡ አድርጓል (፪x)

እንዲህ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲረዳ
እንዲህ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ሲያሳርፍ
(እንዲህ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲረዳ
እንዲህ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ሲያሳርፍ) (፪x)

ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ጌታን ፡ አመልካለሁ
ጌታን ፡ አከብራለሁ (፪x)
እርሱ ፡ የእኔ ፡ አባት ፡ መድሃኒቴ ፡ ነው (፫x)
አቅም ፡ ብርቱ ፡ ሳለ ፡ ጉልበቴ ፡ ሳይደክም
ለዚህ ፡ ከንቱ ፡ ዓለም ፡ ልቤን ፡ አላዝልም
አቅም ፡ ብርቱ ፡ ሳለ ፡ ጉልበቴ ፡ ሳይደክም
ለዚህ ፡ ከንቱ ፡ ዓለም ፡ ልቤን ፡ አላዝልም (፪x)

እንደምን ፡ ይቻላል ፡ ያለ ፡ ጌታ ፡ ሆኖ
በራስ ፡ መተማመን ፡ ድጋፍ ፡ ተሸፍኖ
ዓለምን ፡ ናቅ ፡ አድርጐ ፡ ጌታን ፡ መወዳጀት
ይህ ፡ ታላቅ ፡ ጥበብ ፡ ነው ፡ የሠማይ ፡ በረከት
ዓለምን ፡ ናቅ ፡ አድርጐ ፡ ጌታን ፡ መወዳጀት
ይህ ፡ ታላቅ ፡ ጥበብ ፡ ነው ፡ የሠማይ ፡ በረከት (፪x)

እንዲህ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲረዳ
እንዲህ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ሲያሳርፍ
(እንዲህ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲረዳ
እንዲህ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ሲያሳርፍ) (፫x)


Lirik lagu lainnya:

LIRIK YANG LAGI HITS MINGGU INI

Loading...