lirik.web.id
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

lirik lagu lij michael - mamaye

Loading...

በዘመድ ተከባ በሰፈር ግዛት
ሁሉም ይፈራታል የሴት አንበሲት
እኔም በአንቺ ስም ታማው በሰፈሩ
ስሜ ካንቺ በፊት ነበረ ደፋሩ
ማማዬ ማማዬ ቆንጆ ልጅ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ ቆንጆ ልጅ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ
ገዳም ዋለች አሉ ሄዳ አደረች እዛ
ማማዬ ማማዬ
ኧረ እንዴት ቻለችው የሰውን ልብ ይዛ
ማማዬ ማማዬ
የማማርን ትርጉም የጸዳልን ፍቺ
በማን ላስነግረው ካልሆነማ ባንቺ
ሄደች አቀናችው ልከተላት እኔ
እሷም በቁንጅና ወንድም ልጅ በወኔ
እቴ ተነሽ ተነሽ አምረሽ በሽመና
ለመሬቱም አንቺ ሌላኛው ደመና
እዳለሽ ቆይለት ያማርሽበት ድረስ
የቀባሽን ቅባት እስክናውቅው ድረስ
እቴ ምንሽን ነው ቀኑን የሚያሙሽ
አማረባት ይሆን ካፍ የከተተሽ
እኔ እረፊ ብዬ ተናግሬ ነበር
እንዲ ያማረባትን ቀርቦ ማነጋገር
ሰው አቅም አነሰው ቀኑ እየተናጋ
ስላንቺ ሲናገር ሳይመሽ እየነጋ
ማማዬ ማማዬ ቆንጆ ልጅ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ ቆንጆ ልጅ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ
ገዳም ዋለች አሉ ሄዳ አደረች እዛ
ማማዬ ማማዬ
አረ እንዴት ቻለችው የሰውን ልብ ይዛ
ማማዬ ማማዬ
ድርብብ ያለች ደርባባ የምታምር አበባ
የከተማ ወለባ የተሰራች ሹሩባ
የትልቅ ልጅ ክብርቷ
እቴ የሚሏት በቤቷ
በቤቷ በቤቷ
እንደ ልቤ እንደ ስሜቴ
ለኔስ ያለኝ ባቅም ባንገቴ
የተስማማች ለኔስ አንደኛ
ሁሏ ፍቅር የሆነ ማኛ
ዘመዳ ዘመዱ የኔ የምላቸው
እንዴት ነህ ይሉኛል እንዴት ልበላቸው
አመል ከቁንጅና ለጉድ ተሰጠና
ወንድ ልጅ በከባድ ገጠመው ፈተና
ኧረረረ ያለው ያገር ጀግና
ለካ ተወግቶ ነው ልቡን በቁንጅና
በታችም በላይም ዝናው ሊመታ ነው
ልቤም እሷን ይዞ በዋስ ሊፈታ ነው
ዘመዳ ዘመዱ የኔ የምላቸው
እንዴት ነህ ይሉኛል እንዴት ልበላቸው
ማማዬ ማማዬ ቆንጆ ልጅ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ ቆንጆ ልጅ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ
ገዳም ዋለች አሉ ሄዳ አደረች እዛ
ማማዬ ማማዬ
አረ እንዴት ቻለችው የሰውን ልብ ይዛ
ማማዬ ማማዬ


Lirik lagu lainnya:

LIRIK YANG LAGI HITS MINGGU INI

Loading...