lirik.web.id
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

lirik lagu hanna tekle - regichalew

Loading...

ለሰላሜ የሚሆነኝን አውቄያለሁ አግኝቻለሁ
ለእፎይታዬ የሚበጀኝን አምኛለሁ ተቀብያለሁ
የእግዚአብሔር ልጅ በርቶልኛል በመንፈሱ ረግቻለሁ

ላልወሰድ በምድር ተረት ለዘልአለም ታክሜያለሁ

ከአላማኞች በተሰወረ
ከጠቢባን ዘንድ ባልነበረ
የሞኝነት በሚመስል ታምር
እኔ አርፌያለሁ በአንተ ማመን ሚስጥር

ባንተ ደስ ብሎኛል ፀጋ በዝቶልኛል
ረክቻያለሁ አመሰግናለሁ
ሰላም ረግቶልኛል ፍቅርህ ዘልቆልኛል ረግቻለሁ አመሰግናለሁ

ባንተ ደስ ብሎኛል ጸጋህ በዝቶልኛል ረክቻለሁ አመሰግናለሁ
ሰላም ረግቶልኛል ፍቅርህ ዘልቆልኛል ረክቻለሁ አመሰግናለሁ

የማይነጥፍ ነው ሰላሜ የማያልፍ ነው እረፍቴ
ማደርያህ ለሆን ወደህ ዘልቀሀልና በህይወቴ
የማይደበዝዝ ፍቅር ነው ሽንገላም ወረትም በሌለው
ካንተ ያልተቀበልኩት ምን አለኝ ቀረ ምለው

አንተ ሞልተኸኛል ህይወት በዝቶልኛል ረክቻለሁ ልጅህ ተብያለሁ
ባንተ ደስ ይለኛል ሰላም ረግቶልኛል ረክቻለሁ አመሰግናለሁ

በሰማያዊ በረከት በራስህ ተባርኪያለሁ
እዚህ እንዳልናወጥ ከእቅፍህ ገብቻለሁ
አልሸበርም በአለም በሚሰማው ክፉ ወሬ
ባልከኝ ረግቻለሁ በያዝከኝ እስከዛሬ

አንተን ይዞ ያልረካ ማነው
አንተን ይዞ ያልሰከነ ማነው
አንተን ይዞ የባከነ ማነው
አንተን ይዞ የባዘነ ማነው

ባንተ ደስ ብሎኛል ጸጋህ በዝቶልኛል ረክቻለሁ አመሰግናለሁ
ሰላም ረግቶልኛል ፍቅርህ ዘልቆልኛል ረክቻለሁ አመሰግናለሁ


Lirik lagu lainnya:

LIRIK YANG LAGI HITS MINGGU INI

Loading...