lirik.web.id
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

lirik lagu feven yoseph - sewer fiqir (ስዉር ፍቅር)

Loading...

ስውር አርጎ ቢያስተሳስረው በፍቅሩ
ውብ ሆነና ታየ ማህደሩ ፍጥረቱ
ውብ አርጎ ሰሪው በጥበብ ቢገልጠው
ሰው ግን አላየ ስውሩን ፍቅር ባያውቀው
ነይ ንቢት አንቺ ልባም

ምን አይነት እውነት ምን ሹክ ብለሽው
ወይ ምን አይነት ሚጣፍጥ ፍቅር ሰጥተሽው
በምን ጠቢብ አይኖችሽ ነው ምታዪው
ያንን ግራዋ ጣፋጭ ማር ያረግሽው

ሰው ግን ልቡን ከፍቶ ቢያስተውል በጥበብ
ውብ ሆና ያያታል አለም ስታብብ
ከህልሙ ይደርሳል ቀና ይሆናል መንገዱ
እረፍት ሆኖ ልቦናው እግሩን ሲመራው
ሰው የዋህ አላዋቂ (2~)

ምን አይነት እውነት ምን ሹክ ብለሽው
ወይ ምን አይነት ሚጣፍጥ ፍቅር ሰጥተሽው
በምን ጠቢብ አይኖችሽ ነው ምታዪው
ያንን ግራዋ ጣፋጭ ማር ያረግሽው 2~

ካስተዋለው ሰሪው ሲያበጃጀው
ሁሉን ገምዶ በፍቅር አዋሃደው
ራሱን በጥበብ ቢገልጥ በፍቅር ተሳስሮ
ታየ ሆነው ውብ ተፈጥሮ
ምን አይነት እውነት ምን ሹክ ብለሽው
ወይ ምን አይነት ሚጣፍጥ ፍቅር ሰጥተሽው
በምን ጠቢብ አይኖችሽ ነው ምታዪው
ያንን ግራዋ ጣፋጭ ማር ያረግሽው 2~

ልቤን ልክፈትና ጥበብን ካንቺ ልይ
ንቤ ነይ (3~) ነይ


Lirik lagu lainnya:

LIRIK YANG LAGI HITS MINGGU INI

Loading...