lirik lagu dan admassu - keftosh endalay
ከፋኝ ያንቺን እምባ ካይንሽ ሳየው
አዝኗል ለካስ ልብሽ ደስታም የለው
እንኳን አዝነሽለት ይህን አለም
ስቆም የሚሞላ ከቶ አይደለም
ለሀዘን ፊት አትስጭው ጭራሽ
ህይወት ላትኖሪያት ደግመሽ
ለኔ ደስታዬ ነው ብታይ
ምንም አይኔ ከፍቶሽ ባላይ
ጊዜን ላይገዛው ሰው ላይመልሰው
ቢያዝንም ቢጨነቅ ትርጉም ላይሰጠው
ያልፋል ይሄ ቀን አንቺን ያለፋው
እስከዛ አይንሽ ማንባቱ ይብቃው
ቀኑም ቢጨልም ሰማዩም ቢመሽ
ጠዋት ይሆናል ይነጋል አይዞሽ
ነገን ለሚያስብ ተስፋን ላዘለ
ሲያድር ከዛሬ ሌላ ቀን አለ
ከፍቶሽ እንዳላይ
እንዳላይ
አዝነሽ እንዳላይ
እንዳላይ
ከፍቶሽ እንዳላይ
እንዳላይ
አዝነሽ እንዳላይ
እንዳላይ
ከፋኝ ያንቺን እምባ ካይንሽ ሳየው
አዝኗል ለካስ ልብሽ ደስታም የለው
እንኳን አዝነሽለት ይህን አለም
ስቆም የሚሞላ ከቶ አይደለም
ለሀዘን ፊት አትስጭው ጭራሽ
ህይወት ላትኖሪያት ደግመሽ
ለኔ ደስታዬ ነው ብታይ
ምንም አይኔ ከፍቶሽ ባላይ
ጸሀይ ባትወጣ ቢያይል ደመናው
ቢከብድሽ እንኳን እሾህ ጋሬጣው
ለቀን አለቃም ቀን አለውና
አሮጌው በአዲስ ይተካል ገና
ቀኑም ቢጨልም ሰማዩም ቢመሽ
ጠዋት ይሆናል ይነጋል አይዞሽ
ነገን ለሚያስብ ተስፋ ላዘለ
ሲያድር ከዛሬ ሌላ ቀን አለ
ከፍቶሽ እንዳላይ
እንዳላይ
አዝነሽ እንዳላይ
እንዳላይ
ከፍቶሽ እንዳላይ
እንዳላይ
አዝነሽ እንዳላይ
እንዳላይ
ከፍቶሽ እንዳላይ
እንዳላይ
አዝነሽ እንዳላይ
እንዳላይ
ከፍቶሽ እንዳላይ
እንዳላይ
አዝነሽ እንዳላይ
እንዳላይ
Lirik lagu lainnya:
- lirik lagu dante bowe - all god’s children
- lirik lagu piso 21 - tan bonita
- lirik lagu hedgi - fool for trusting you
- lirik lagu massa - benji
- lirik lagu genghis tron - alone in the heart of the light
- lirik lagu robot95 - sol
- lirik lagu lana del rey - angel city [unreleased]
- lirik lagu otzeki - sweet sunshine
- lirik lagu distorted harmony - awaken
- lirik lagu disciples - solid gold