lirik lagu abenet agonafer - smigne
እስካገኝሽ ችዬ
እንዲገባሽ ብዬ
አምነሽ ብትመቺ እያልኩ
ናፍቄ እየቻልኩኝ
ስትሸሺኝ አጥፍተሽ
ተከትዬ ባቅፍሽ
ምን ሊጠቅምሽ
ምን ሊጠቅምሽ
ለማለፍ ያቺን ቀን
ሊደገም ቀን በቀን
ምን ሊጠቅምሽ
ምን ሊጠቅምሽ
ባዝንም ሌላው ቢያስከፋኝ
ማለፍ መተው መች ጠፋኝ
አንቺን አላልፍም የኔን ካላየሽ
ከፍቶሽ መጥቼ ከፍቶኝ ካልመጣሽ
የፍቅር ቅሬታዬን የመውደድ ዝምታዬን
ደልቶኝ መች አቀፍኩት
እስክትመጪልኝ ነው ያፈንኩት
ዝም አልልም ደፍሬ
ላስከፋሽ እኔ አንቺን አፍሬ
የቃልነው ላይ ኪሳራ
ለልብ ወዳጅ ላይሰራ
ናፍቆታሽ ቢያመኝም
ሸንግዬሽ በርሽን አልከፍትም
ልቤ ይዝጋላሽ ፍቅሬ
ቢስምሽ ትርፍ ነው ከንፈሬ
ስሚኝ ስሚኝ ስሚኝ
እስካገኝሽ ችዬ
እንዲገባሽ ብዬ
አምነሽ ብትመቺ እያልኩ
ናፍቄ እየቻልኩኝ
ስትሸሺኝ አጥፍተሽ
ተከትዬ ባቅፍሽ
ምን ሊጠቅምሽ
ምን ሊጠቅምሽ
ለማለፍ ያቺን ቀን
ሊደገም ቀን በቀን
ምን ሊጠቅምሽ
ምን ሊጠቅምሽ
አንዴ ስሚው ይንገርሽ
ያውቃል እውነቱን ልብሽ
የኔም ልብ ያውቃል ያንቺ ያየውን
አልሰማ አላቸው እንዳይለያዩን
የፍቅር ቅሬታዬን
የመውደድ ዝምታዬን
ደልቶኝ መች አቀፍኩት
እስክትመጪልኝ ነው ያፈንኩት
ዝም አልልም ደፍሬ
ላስከፋሽ እኔ አንቺን አፍሬ
የቃልነው ላይ ኪሳራ
ለልብ ወዳጅ ላይሰራ
ናፍቆታሽ ቢያመኝም
ሸንግዬሽ በርሽን አልከፍትም
ልቤ ይዝጋላሽ ፍቅሬ
ቢስምሽ ትርፍ ነው ከንፈሬ
ስሚኝ ስሚኝ ስሚኝ
ኦኦኦኦኦኦው
ደልቶኝ መች አቀፍኩሽ
እስክትመጪልኝ ነው ያፈንኩት
ዝም አልልም ደፍሬ
ላስከፋሽ እኔ አንቺን አፍሬ
ናፍቆታሽ ቢያመኝም
ሸንግዬሽ በርሽን አልከፍትም
ልቤ ይዝጋላሽ ፍቅሬ
ቢስምሽ ትርፍ ነው ከንፈሬ
Lirik lagu lainnya:
- lirik lagu astéréotypie - les dates dans ma tête
- lirik lagu hailey whitters - gone country (apple music sessions)
- lirik lagu lil kori - hentai gang anthem
- lirik lagu sebastián cortés - todo ha cambiado para siempre
- lirik lagu francesco paolo tosti - o ma charmante
- lirik lagu aarya - that guy
- lirik lagu alex chou (周予天) - smoke
- lirik lagu arlie - findaway
- lirik lagu callaway redd - can't love
- lirik lagu axelence - chérie